የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ታሪካዊ አመጣጥ

I.     ኢሚግሬሽን በኢትዮጵያ

1.  ድመ

ከ19ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የኢሚግሬሽን አገልግሎት ይሰጥ ነበር ማለት አያስችልም፡፡ ይሁንና የውጭ ሃገር ዜጐች ከንጉሰ ነገስቱ በሚሰጥ ፈቃድ ወደ አገር መግባትና በአግር ውስጥ መቆየት ፈቃድ ይሰጥ ነበር፡፡ ጉብኝታቸውን ከጨረሱ በኃላ በመጡበት እንዲመለሱ ይደረግ እንደነበረ ታሪክ ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያት ማለት ለህክምና፣ ለወታደራዊ አማከራዎች እና ለሚሽንሪዎች በተፃፈ ደብዳቤ ፈቃድ ይሰጥ ነበር፡፡

ይህ የኢሚግሬሽን አገልግሎት በዘመናዊ መልክ የተደራጀ አሰራር ያልነበረው ቢሆንም ከ1879 ዓ.ም ጀምሮ አሰራሩን በመጠኑ ተቋማዊ ለማድረግ የተጀመረበትና ወደ ሀገር የሚገቡ የውጭ ሃገር ዜጐች ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ንጉሰ ነገስቱ (ከአፄ ዮሃንስ አራተኛ) በሚፈቀደው ፈቃድ መሠረት የንጉሱ ፊርማ ያረፈበት የፈቃድ ደብዳቤ ለአገር ገዥዎች (አስተዳዳሪዎች) እንዲያውቁት ተደርጐ የውጭ ዜጋው ከመግቢያ በር ጀምሮ ንጉሱ ያሉበት ከተማ ድረስ እንዲመጡ ሲደረግ የውጭ ሃገር ዜጋው በጉዞው ወቅት በየደረሰበት ሥፍራ ሁሉ ያሉ አስተዳዳሪዎች እያስተናገዱት ደህንነቱን ጠብቀው በቅብብሎሽ የሚያደርሱት ሲሆን በዚህ ጉዞ ወቅት የውጭ ዜጋውን እያስተናገደ፣ ማደሪያ እየሰጠ እና እየመገበ በበቅሎ አጓጉዞ የማድረስ ሃላፊነት የአካባቢው አስተዳደሮች ላይ የተጣለና የውጭ ዜጋውን በመንገዱ ላይ አደጋ እንዳይደርስበት እና ከአውሬ እየጠበቀ የማድረስ ግዴታ ተጥሎበት ነበር፡፡

የውጭ ሃገር ዜጋውም ከላይ በተጠቀሰው መልኩ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ የመጣበትን ሥራ ጨርሶ ሲወጣ በተመሳሳይ መልኩ ከሀገር እንዲወጣ ከንጉሰ ነገስቱ የመውጫ ደብዳቤ ተሰጥቶት በገባበት በር በኩል እንዲወጣ ይደረግ ነበረ፡፡ ሂደቱ እንደ ቀጠለ ሆኖ ከአፄ ዮሃንስ አራተኛ በኃላ የመጡት አፄ ሚኒሊክ በ1900 ዓ.ም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በአዋጅ ሲቋቋሙ ይኸው የኢሚግሬሽን ቢሮ አደረጃጀቱ በአገር ግዛት ሚኒስቴር ሥር የፀጥታ ዴሬክሲዩን ተብሎ በሚጠራው የሥራ ክፍል ውስጥ አንድ ክፍል ሆኖ የተዋቀረ ሲሆን ይኸውም አወቃቀር ወይም አደረጃጀት በዘመነ ኃይለስላሴ ጊዜም በተመሳሳይ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎ ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ በኋላ በ1934 ዓ.ም የኢሚግሬሽን አዋጅ የወጣ ቢሆንም አደረጃጀቱ ሳይቀየር በክፍል ደረጃ የነበረና የሰው ሃይሉ አደረጃጀቱም በጣም አነስተኛ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይገልፃሉ፡፡

ከ1966 ዓ.ም የንጉሳዊ ስርዓቱ መውደቅ በኋላ ደርግ ስልጣኑን እንደያዘ በህዝብ  ደህንነት ጥበቃ መሥሪያ ቤት ስር “የይለፍ ክፍል” ተብሎ እስከ 1972 ዓ.ም ድረስ እየሰራ እያለ ከ1972 ዓ.ም መጨረሻ እሰከ 1980 ዓ.ም ባለው ጊዜያት ወደ መምሪያ ከፍ በማድረግ ስያሜውንም የይለፍና ኰንስለር መምሪያ በማለት እንዲዋቀር ተደርጐ ሲሰራ ከቆየ በኋላ በ198ዐ ዓ.ም አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ተብሎ በሚኒስቴር ደረጃ ሲቋቋም ቀደም ተብሎ ሲጠራበት የነበረው ስም ተቀይሮ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ዋና መምሪያ ተብሎ በዋና መምሪያ ደረጃ እንዲቋቋም ተደርጐ ነበር፡፡

ይህ የኢሚግሬሽን ታሪካዊ ሂደት የነበረ ሲሆን ይህ አሰራር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና አለም የደረሰበት ሁኔታ ጋር አሰራሩን ማዘመን በማስፈለጉ በአሁኑ ጊዜ ዋና መምሪያው  አደረጃጀቱን በማሻሻል ወቅቱ የሚጠይቀውን ዘመናዊ የኢሚግሬሽን አሰራር በመከተል ቀደም ሲል ማንዋል ፖስፓርት ይሰጥ የነበረውን በማስቀረት ኤሌክትሮኒካል ፖስፓርት መስጠት መጀመሩ ይህንን ተግባር ለማከናወን በርካታ ዘመናዊ መሳሪያዎች በማስገባት (በመትከል) የራሱ የፖስፓርት ህትመት ማተም ችሏል፡፡

2.    ድሕረ

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት የሆኑት የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በነፃ ፍላጐታቸው ተወካዮቻቸውን ልከው ባፀደቁት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ሕገ መንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987 በስራ ላይ ሲውል ከፍተኛውን ቦታ የያዘው መሠረታዊ የሆኑ የዜጐችን መብቶች እና ነፃነቶችን ሲሆን፣ በስፋት ከተዘረዘሩት የዴሞክራሲ መብቶች ውስጥ የመዘዋወር ነፃነትን መብት ዘርዝሮ ያስቀምጣል፡፡ በተጨማሪም በሕገ መንግሥቱ ጠቅላላ ድንጋጌ ውሰጥ ኢትዮጵያ ዜጋ የሆነን እና የውጭ ሐገር ዜጐች የኢትዮጵያን ዜግነት ሊያገኙ የሚቻልበትን ሁኔታ ዘርዘር ባለ ሁኔታ በግልጽ ደንግጓል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ግዙፍ ዴሞክራሲያዊ መብቶች እና ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ማስተናገድ እንዲያስችል የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ በሕግ አግባብ ተቋቁሞ በግልጽ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህንን ሕገ መንግስታዊ መብት ከተቋሙ ተልእኮ ጋር ሊጣጣም በሚችል መልኩ ለኢትዮጵያዊያን እና ለውጭ ሐገራት ዜጐች ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ደህንነቱን የጠበቀ የኢሚግሬሽን አገልግሎትን መስጠት ሲሆን በተጨማሪም፡-

·       ሕጋዊ የሰዎችን እንቅስቃሴ ማረጋገጥ፤

·       የተለያዩ የይለፍ ሰነዶችን ወይም ቪዛዎችን  ለመንግስት መ/ቤቶች ተቀጣሪ እና ለአጫጭር ስራዎች፣ ለግል ድርጅት ተቀጣሪ፣ ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ተቀጣሪ፣ ለውጭ ባለሐብት ተቀጣሪ፣ ለትርፍ ላልተቋቋመ ድርጅት፣ ለሚዲያ ወይም ጋዜጠኛ፣ ለአጭር ስብሰባ፣ ለኢንቨስትመንት፣ የቱሪስት እና የትራንዚት ቪዛ አገልግሎትን መሰጠቱን ማረጋገጥ፤

·       የጉዛ ሰነድ እንደ መደበኛ ፓስፖርት፣ አንድ ግዜ የይለፍ ሰነድ፣ አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ እና የስደተኞች የጉዞ ሰነድ አገልግሎት በአግባቡ መሰጠቱን ማረጋገጥ፤

·       ጥምር ዜግነትን ፈቃጅ ያልሆነው የኢትዮጵያ የዜግነት አዋጅ ቁጥር 378/1996  በተጨማሪም ሌሎች ተዘርዝረው የወጡትን ሕጐች የማክበር እና የማስከበር እንዲሁም ከዜግነት ጋር በተያያዙ የሚቀርቡ አቤቱታ እና ጥያቄዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመመርመር ውሳኔ እንዲያገኝ ማድረግ፣

·       በኢሚግሬሽን አዋጅ ቁጥር 354/1995 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የውጭ ዜጐች ምዝገባ አና ቁጥጥር ማድረግ ሕጋዊነታቸው ሲረጋገጥ የመኖሪያ ፍቃድ መስጠት በሌላ በኩል ሐገሪቱ ያወጣችውን ሕግ እና ደንብ ባላከበሩ በውጭ ሐገር ዜጐች ላይ በሕጉ መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ እና መከታተል፣

·       በኑሮና በሕይወት አጋጣሚዎች እንዲሁም በተለያዩ ምክንያት የኢትዮጵያ ዜግነትን በመተው የሌላ ሐገር ዜግነት የወሰዱ እና የኢትዮጵያ ዜግነታቸው በመቅረቱ ለወገኖቻቸው ኑሮ መሻሻል ለትውልድ ሐገራቸው እድገትና ብልጽግና የበኩላቸውን የሚያደርጉትን አስተዋፆ የህግ ማእቀፍ ለማላላት በአዋጅ ቁጥር 270/1994 የወጣውን የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐችን በትውልድ ሐገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ የሚያደርገውን አምስት ዓመት አገልግሎት ያለውን የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ በሐገር ውስጥ እና  በሚሲዮኖች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

·       አገልግሎቱን በአገር ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ ከዋና መምሪያው ጋር በሲስተም የተገናኙ 6 (ስድስት) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመክፈት ለዜጐች ፖስፓርትና ለውጭ ሃገር ዜጐች የቪዛ ማራዘሚያ እና የሃገር ውስጥ መኖሪያ ፈቃድ እና የእድሳት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በውጭ ሃገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች የቆንስላ አገልግሎት ማለት የፖስፖርት፣ የትውልድ መታወቂያ በማእከል ተዘጋጅተው ለባለጉዳዮች እንዲደርሱ ያደርጋል የተለያዩ ቪዛዎችም ወደ ሃገር ለሚገቡ የውጭ ሃገር ዜጐች በሚሲዮኖች እና በመግቢያ በሮች ላይ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

·       በአየርና በየብስ ኬላዎች ከዋናው መምሪያ ጋር በሲስተም በተገናኙ የአየርና የየብስ ኬላዎች ላይ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በመድረሻ ላይ ቪዛ ለተፈቀደላቸው አገሮች የመድረሻ ቪዛ ይሰጣል እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ሲከናወን በሲስተም የታገዘና አገልግሎቱ የተሰጣቸው ሁሉ መረጃቸው በዳታ ቤዝ እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡

ራዕይ እና ተልዕኮ

ራዕይ

የምንሰጠውአገልግሎትዓለምአቀፍደረጃውንየጠበቀ፣      የህዝቦችሰላማዊእንቅስቃሴንደህንነትያረጋገጠናየሀገሪቷን እድገትያፋጠነ ሆኖ ማየት፡፡      

ተልዕኮ

ህጋዊ የሰዎች እንቅስቃሴ ማረጋገጥ፣ የይለፍ ሰነድ፣የዜግነት መስጠትና ቁጥጥር ማካሄድ፡፡